Muslima የማህበረሰብ መመሪያዎቻችንን

Muslima ደህንነቱ የተጠበቀ የኢንተርኔት መቀጣጠሪያ አገልግሎት (ገጽ) በማቅረቡ ኩራት ይሰማዋል። አባላት እርስ በርስ ግንኙነት ሲያደርጉና አገልግሎታችንን ሲጠቀሙ እርስ በርሳቸው እንዲከባበሩና እንዲተሳሰቡ እናበረታታለን።

እነዚህ የማህበረሰብ መመሪያዎች ከእኛ የአጠቃቀም ድንጋጌዎች ጋር በጥምረት መነበብ አለባቸው። ማንኛውም እነዚህን የማህበረሰብ መመሪያዎች የሚጥስ ሰው ካጋጠምዎ እባክዎ ይህን በአስቸኳይ ሪፖርት ያድርጉልን። የማህበረሰብ መመሪያዎቻችንን መጣስ የሚያስከትላቸው ውጤቶች እንደ ጥሰቱ ክብደት ላይ እና የአባሉ የቀዳሚ ጊዜ ባህሪ ላይ ተመስርቶ ይለያያል። በማህበረሰብ መመሪያዎቻችን ላይ የሚፈጸም ከባድ ጥሰት የጥፋተኛውን አባል አካውንት እስከ ማቋረጥ እና/ወይም አገልግሎታችንን ከመጠቀም እስከ ማገድ የሚደርስ ቅጣት ያስቀጣል።

የእኛ የማህበረሰብ መመሪያዎች የሽፋን ገጽ

  • የግል መረጃ ይዘት እና አጠቃቀም
  • የግል ፎቶዎች
  • ግንኙነት
  • አካውንት/የግል መረጃ ደህንነት

የግል መረጃ ይዘትና አጠቃቀም

ብቁነት

ለመመዝገብ እና አገልግሎታችንን ለመጠቀም እድሜዎ ከ18 አመት በላይ መሆን አለበት።

የግል መረጃ ትክክለኛነት

አባላት እራሳቸውን በተመለከተ ትክክለኛ የግል መረጃ እንዲያቀርቡ እናበረታታለን። የትኛውንም ሌላ ሰው መስለው መቅረብ፣ እድሜዎን ወይም የጋብቻ ሁኔታዎን ማሳሳት፣ ወይም በግል መረጃዎ ላይ በየትኛውም መልኩ ሀሰተኛ ወይም አሳሳች መረጃ ማስገባት የለብዎትም።

ብቁነት

የግል መረጃዎ (ስምዎን፣ የግል መረጃዎ ርዕስን እና የግል መረጃዎ ዝርዝርን ጨምሮ) ጠብ አጫሪ፣ ጥላቻ፣ ፀያፍ፣ ህገወጥ ወይም ያልተገባ ይዘት መያዝ የለበትም። የግል መረጃዎ ሽብርተኝነትን የሚያስፋፋ፣ ስለ ፖለቲካ የሚያብራራ፣ ጥቃትን ወይም በራስ ላይ የሚፈጸም ጉዳትን የሚያበረታታ ይዘት መያዝ የለበትም።

የግል መረጃ ልዩ መሆን

ከአንድ በላይ አካውንቶች/የግል መረጃ ገጾች መፍጠር የለብዎትም። እኛ በምናንቀሳቅሰው በአንድ ድረገጽ መክፈት የሚፈቀድልዎ አንድ ብቻ ልዩ የግል መረጃ ገጽ ነው። ተደጋጋሚ የግል መረጃ ገጾችን እናቋርጣለን።

የግል መረጃ አላማ

የግል መረጃዎ እውነተኛ የፍቅር ጓደኛ ወይም ጥንድ ለመፈለግ አላማ ብቻ ጥቅም ላይ መዋል አለበት። እውነተኛ የፍቅር ጓደኛ ወይም ጥንድ ለመፈለግ አላማ የማያገልግል የግል መረጃን እናቋርጣለን። በግል መረጃዎ ላይ የትኛውንም የገንዘብ፣ ስጦታ ወይም የገንዘብ ዋጋ ያለው ጥያቄ የሚያነሳሳ ይዘት መኖር የለበትም። ‹‹በእድሜ የገፋ ሰው›› የፍቅር ግንኙነቶች ለመመስረት፣ ጥሎሽ/ እጅ መንሻ ለማቅረብ ወይም ለተመሳሳይ አላማዎች የሚያገለግሉ የግል መረጃዎችን አንፈቅድም። በአንዳንድ ድረገጾቻችን የተወሰኑ ግዛቶች ህግን ላለመተላለፍ የጋብቻ ጓደኛ ለመፈለግ የሚያገለግሉ የግል መረጃዎችን ላንፈቅድ እንችላለን።

የግል መረጃ ባለቤትነት

የግል መረጃዎ በራስዎ ብቻ ለመጠቀም መከፈት አለበት። በግል መረጃዎ ሌሎች ሰዎች እንዲጠቀሙ መሸጥም ይሁን ለሌላ ሰው ማስተላለፍ አይችሉም።

ፎቶዎች

የሚጭኗቸው ፎቶዎች ትክክለኛና በየትኛውም መልኩ ጉዳት የማይፈጥሩ መሆን አለባቸው። የሚያስገቧቸው ፎቶዎች የራስዎ መሆን አለባቸው።

ከታች የተመለከቱትን የሚይዙ ምስሎች ማስገባት የለብዎትም:

  • ከራስዎ ውጭ ማንኛውንም ሌሎች ሰዎች የሚይዙ
  • እርቃን አካል የሚይዙ
  • ከልክ ባለፈ መልኩ ወሲብ ቀስቃሽ የሆኑ
  • አመጽን የሚያገኑ
  • በየትኛውም መልኩ የግንኙነት መረጃ የያዙ
  • አግባብነት የሌላቸው
  • ህጻናትን የሚይዙ
  • የሌላ ሰው የቅጂ መብት ጥያቄ የሚያስነሱ

የትኛውም እነዚህን ሁኔታዎች መጣስ ፎቶው ተቀባይነት እንዳያገኝ ያደርጋሉ። በአንዳንድ ሁኔታዎች የግል መረጃ (አካውንት) እንዲቋረጥ ሊያደርጉ ይችላሉ።

ግንኙነት

ከሌላ የደንበኛ አገልግሎት ጋር የሚደረግ ግንኙነት

የደንበኞች አገልግሎት ሰራተኞቻችንን በሚያነጋግሩበት ወቅት የጥቃት፣ አናዳጅ፣ ስሜት የሚጎዳ፣ የስድብ፣ የዛቻ ወይም የዘር ጥቃት አዘል ምግባር/ቃላት መጠቀም የለብዎትም

በጥቃት ምግባር ላይ የሚሳተፉ ከሆነ አባልነትዎን በአስቸኳይ የማቋረጥ መብት አለን።

ከሌሎች አባላት ጋር የሚደረግ ግንኙነት

በኢንተርኔት ወይም ከኢንተርኔት ውጭ ሌሎች አባላትን በሚያነጋግሩበት ወቅት የጥቃት፣ አናዳጅ፣ ስሜት የሚጎዳ፣ የስድብ፣ የዛቻ ወይም የዘር ጥቃት አዘል ምግባር/ቃላት መጠቀም የለብዎትም። የትኛውንም ያልተፈቀዱ ለወሲብ አነሳሽ የጽሁፍ መልዕክቶች መላክ የለብዎትም። የትኛውንም ሽብርተኝነትን የሚያስፋፉ፣ ጥቃትን ወይም በራስ ላይ የሚፈጸም ጥቃትን የሚያረታቱ የጽሁፍ መልዕክቶችን መላክ የለብዎትም። ለሴተኛ አዳሪነት ወይም ህገወጥ የሰዎች ዝውውር የሚያነሳሳ ግንኙነት ማድረግ የለብዎትም። አገልግሎቶች ወይም ምርቶችን የሚያስተዋውቁ አላስፈላጊ የኢሜይል፣ የጽሁፍ መልዕክቶች፣ ወይም አገልግሎት ወይም ምርትን ለማስተዋወቅ አላማ የየትኛውንም የውጭ ድረገጾች የግንኙነት አድራሻዎች የሚያቀርቡ የጽሁፍ መልዕክቶች መላክ የለብዎትም። ይህ የትኛውንም አይነት የንግድ ድርጅቶች፣ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወይም ማህበራትን ማስተዋወቅን ያጠቃልላል።

ከየትኛውም ህገወጥ ድርጊት ጋር ተያያዥነት ያለው ግንኙነትን ለሚመለከተው የህግ አስፈጻሚ ድርጅት ሪፖርት ልናደርግ እንችላለን።

ትንኮሳ

አገልግሎቱን የትኛውንም አይነት የወሲብ እና/ወይም የዘር ጥቃት፣ ጥቃት፣ ትንኮሳ፣ ጋጠወጥነት፣ ስሜት ጎጂ፣ ትንኮሳ፣ ጠብ አጫሪነት፣ ስም የሚያጎድፍ ወይም ተቀባይነት የሌለው መረጃ ማሰራጨትን ጨምሮ በእነዚህ ላይ ብቻ ሳይወሰን በየትኛውም የትንኮሳ ወይም ጥቃት ባህሪ ላይ ለመሳተፍ በፍጹም መጠቀም የለብዎትም። ከየትኛውም ከዘጉዎ ወይም ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንደማይፈልጉ የገለጹልዎት ሰዎች ጋር በተደጋጋሚ ግንኙነት ማድረግ የለብዎትም። ሌላ አባልን እንደ መተንሻ ዘዴ ከአንድ በላይ አካውንት/የግል መረጃ ገጽ መክፈት የለብዎትም።

ለአካለ መጠን ካልደረሱ ልጆች ጋር ግንኙነት ማድረግ የለብዎትም

ሁሉም የሚመዘገቡ ወይም አገልግሎቶቻችንን የሚጠቀሙ ሰዎች እድሜያቸው ከ18 አመት በላይ መሆን አለበት። ለአካለ መጠን ላልደረሱ ልጆች ጥበቃ ማድረግ ያስችለን ዘንድ ተጨማሪ ፖሊሲዎችን ተፈጻሚ እናደርጋለን።

ከየትኛውም ለአካለ መጠን ካልደረሰ ሰው ጋር ያልተገባ ወይም ወሲባዊ ባህሪ አዘል ግንኙነት አያድርጉ። ይህ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ጓደኞችን፣ ዘመዶች ወይም ለአካለ መጠን የደረሱና የድረገጹ አባል የሆኑ የስራ ባልደረቦችን ያጠቃልላል። ይህን ድረ ገጽ ከየትኛውም ለአካለ መጠን ያልደረሰ ሰው ጋር ጓደኝነት፣ የፍቅር ግንኙነት ወይም ያልተገባ ግንኙነት ለመመስረት አላማ ይህን ሰው ድረገጹን እንዲጠቀም ጥቆማ ለመስጠት መጠቀም የለብዎትም።

የትኛውንም ህገወጥ ወይም ያልተገቡ ግንኙነቶች፣ ወይም ያልተገባ ባህሪ ዝርዝሮች ለሚመለከተው የህግ አስፈጻሚ ድርጅት ሪፖርት ልናደርግ እንችላለን።

የግል መረጃ ደህንነት

የጥሩ የደህንነት ስምምነቶችን የማያከብሩ አባላት ሌሎች አባላትን ለተንኮል ድርጊቶች ያጋልጣሉ እንዲሁም የሌሎች አባላት መጥፎ ባህሪያትን ያበረታታሉ። ሁልጊዜም የግል መረጃዎን ደህንነቱ በተጠበቀና አስተማማኝ አኳኋን መጠቀም አለብዎ። ይህ ለእነዚህ የግንኙነት መመሪያዎች ተገዢ መሆንን ያጠቃልላል።

ገንዘብ መላክ

ለየትኛውም ግንኙነት ለሚያደርጉት ወይም በእኛ አገልግሎት አማካኝነት ለሚገናኙት ሰው ገንዘብ መላክ ወይም ገንዘብ ነክ/የፋይናንስ መረጃ መላክ የለብዎትም።

የትኛውም ሰው ገንዘብ ለመጠየቅ ወይም የገንዘብ ነክ መረጃ ለማግኘት ሙከራ ካደረገ ይህን በአስቸኳይ ሪፖርት ያድርጉልን።

መጠየቅ/ማባበል

ይህን አገልግሎት የትኛውንም የገንዘብ ማባበያ፣ የእቃዎች ማስተዋወቂያ ወይም ማባበያ መረጃን ለማሰራጨት፣ ለማስተዋወቅ ወይም ለማተም መጠቀም የለብዎትም። ይህን ማድረግ የግል መረጃዎ እንዲቋረጥ ያደርጋል።

የድረገጹ ደህንነትና ተደራሽት

የሚስጥር መግቢያዎን ለሌላ ሰው መስጠት ወይም ማንኛውም ሌላ ሰው የግል መረጃዎን እንዲጠቀም፣ ወይም የትኛውንም የግል መረጃዎን አደጋ ላይ የሚጥል ነገር እንዲያደርግ መፍቀድ የለብዎትም።

የየትኛውንም የኮምፒውተር ሶፍትዌር ወይም ሀርድዌር አሰራር ለማጥፋት ወይም ለመገደብ ታስበው የተዘጋጁ ቫይረስ ወይም ሌሎች የኮምፒውተር ኮዶች፣ ፋይሎች፣ ወይም ፕሮግራሞች የሚይዙ ግብአቶችን ፖስት አያድርጉ ወይም አያሰራጩ።

በዚህ አገልግሎት ላይ ለመመዝገብ ወይም ለመጠቀም የሰው ያልሆኑ ወይም አውቶማቲክ መግቢያዎችን አይጠቀሙ።

የግል መረጃ አለመንቀሳቀስ

በየተወሰነ ወቅት የማይንቀሳቀሱ የግል መረጃዎችን እናቋርጣለን። የግል መረጃዎ እየሰራ መሆኑን እና አለመቋረጡን ለማረጋገጥ በየወቅቱ መመዝገብዎን ያረጋግጡ።

ጥቃትን ወይም በማህበረሰብ መመሪያዎቻችን ላይ የሚፈጸም ጥሰትን ሪፖርት ማድረግ

ጠቃትን ወይም በማህበረሰብ መመሪያዎቻችን ላይ የሚፈጸም ጥሰትን የእኛን የግንኙነት ቅጽ በመሙላት ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ። በተጨማሪም እነዚህን አባላት በቀጥታ ከግል መረጃቸው ወይም የጽሁፍ መልእክታቸው ላይ ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ። ጥቃትን እንዴት ሪፖርት እንደሚያርጉ በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎ የእኛን የኢንተርኔት እርዳታ ገጽ ይመልከቱ።

ስለ ሌላ አባል ሪፖርት በሚያደርጉበት ወቅት እባክዎ ስለ አባሉ የሚችሉትን ያል መረጃና ማስረጃ ያቅርቡ።

ደህንነትን መጠበቅን የተመለከተ ተጨማሪ መረጃ

ስለ መቀጣጠሪያ ደህንት በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎ የእኛን ድረገጽ በ: http://www.onlinedatingsafetytips.com ይመልከቱ።

ለተጨማሪ መረጃ፣ ድንጋጌዎችና ፍቺዎች እባክዎ

እባክዎ የእኛን የአጠቃቀም ድንጋጌዎች እና የግላዊነት መግለጫ ይመልከቱ።